Full course description
የጨቅላ ህጻናት እና ህጻናት አእምሮ ከአካባቢያቸው ጋር ግንኙነት በመፍጠር በፍጥነት እና በከፍተኛ ጥራት እያደገ ነው፡፡ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ፣ በአሳዳጊዎች እና በጨቅላ ህጻናት መካከል ያለውን ማህበራዊ ግንኙነትና የቋንቋ መስተጋብር ለማበልጸግ ጠቃሚ ጊዜ ነው። ብዙ ጥናቶች የቀደመና የበለጸገ የቋንቋ መስተጋብር ማህበራዊ፣ ስሜታዊ፣ ትምህርታዊና የጤና ውጤቶች ላይ ያለውን ተጽእኖ መዝግበዋል። የሕፃኑ የመጀመሪያዎቹ ሶስት አመታት በአእምሮ እድገት ላይ ወሳኝ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የበለፀገ የቋንቋ መስተጋብር ማግኘት ጠንካራ የቋንቋ እና የቃላት መሰረትን ያመጣል፣ ይህም ለቀጣዩ ህይወት ወደ ተሻለ ማንበብና መጻፍ ይመራል።
ልጄ አናግረኝ በአሜሪካ ውስጥ በኢሞሪ ዩኒቨርሲቲ የነርሲንግ ትምህርት ቤት፣ በኤሞሪ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት፣ በጆርጂያ በህብረተሰብ ጤና ክፍል፣ የአትላንታ የሕፃናት ጤና አጠባበቅ፣ የማርከስ ኦቲዝም ማእከል፣ የሮሊንስ የቋንቋ እና ማንበብ ማእከል በአትላንታ ንግግር ትምህርት ቤት፣ የጆርጂያ ንባብ ያግኙ እና የጆርጂያ የትምህርት ክፍል ተባባሪነት የተጀመረ ነው። ይህ ተነሳሽነት/አላማ በህጻናት የመጀመሪያ እድገት ላይ በቋንቋ/ቃላት የበለጸጉ ግንኙነቶች በአእምሮ እድገት ላይ ስለሚኖረው ተፅእኖ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ያሳድጋል።